Menu Close

የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬና ጤናማ የፋይናንስ ሥርዓት እንዲኖር ይሠራል

የተረጋጋ ዋጋና የውጭ ምንዛሬ እንዲሁም ጤናማ የፋይናንስ ሥርዓት የማክሮኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት በመሆናቸው የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ እነርሱ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ አዲሱ የባንኩ ገዥ አቶ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ ገለጹ፡፡ ከፋይናንስ ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች ጋርም በዘርፍ የ 6 ወር አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

የተረጋጋ ዋጋና የውጭ ምንዛሬ እንዲሁም ጤናማ የፋይናንስ ሥርዓት የማክሮኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት በመሆናቸው የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ እነርሱ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ አዲሱ የባንኩ ገዥ አቶ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ ገለጹ፡፡ ከፋይናንስ ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች ጋርም በዘርፍ የ 6 ወር አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ጥር 24 ቀን 2015 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ህንፃ ዋናው አዳራሽ በተካሄደው ውይይት ላይ አቶ ማሞ የፋይናንስ ዘርፉ ብቻውን የቆመ ሳይሆን ከማክሮኢኮኖሚ ጋር ተያይዞ የሚጓዝ መሆን እንዳለበት አመልክተዋል፡፡ በዚህ ዓመት በ 7 ነጥብ 5 በመቶ ያድጋል ተብሎ ለሚጠበቀው የአገሪቱ ኢኮኖሚ የፋይናንስ ሴክተሩ የራሱ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ጠቁመዋል፡፡ የባንኩ ዋነኛ ተልዕኮዎች የሆኑትን ዋጋ የማረጋጋትና የውጭ ምንዛሬ ተመን የማስፈን እንዲሁም ጤናማ የፋይናንስ ሥርዓት የመፍጠር ጥረት በቀጣይ የባንኩ ዋነኛ ትኩረቶች እንደሚሆኑ የጠቆሙት አቶ ማሞ፣ በቀጣይም የዋጋ ንረትን እንዳያባብስ በገንዘብ ፖሊሲው አማካኝነት የተጠና ሥራ እንደሚሠራም አስታውቀዋል፡፡ የፋይናንስ ዘርፉ በአጠቃላይ፣ በተለይም የባንክ ዘርፉ በአገር ዕድገት ላይ እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ ያነሱት ዋና ገዥው፣ ለአብነትም ባለፉት ስድስት ወራት ከ157 ቢሊዮን ብር በላይ የግምጃ ቤት ሰነድ መግዛቱን አመልክተዋል። ይህም የበጀት ጉድለትን በመሙላት ረገድ የፋይናንስ ዘርፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ ያለው አስተዋጽኦ እየጨመረ መሆኑን እንደሚያሳይ የጠቆሙት አቶ ማሞ፤ ባንኮች የሚሰበስቡት የተቀማጭ ገንዘብ፣ ሃብትና የሚሰጡት ብድር በየዓመቱ በአማካይ በ30 በመቶ እያደገ ስለመሆኑም ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ከባንክ ውጭ ያለው ገንዘብ ከ189 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ጠቁመው ይህም ለባንኮች ተጨማሪ ሃብት ለማሰባሰብ እድል የሚፈጥር እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

More Posts

የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የቦርድ አባላት ሥራ ጀመሩ

በቅርቡ ወደ ሥራ እንደሚገባ ይጠበቅ የነበረውን የካፒታል ገበያ ባለሥልጣንን የሚያገለግሉ ስድስት የቦርድ አባላት ኅዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም. መሾማቸው ይታወቃል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል።

የባንኩ ሠራተኞች 127ኛውን የአድዋ ድል በዓል አከበሩ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሠራተኞችና የማኔጅመንት አባላት 127ኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት አከበሩ። የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በባንኩ አዳራሽ በተከናወነው ሥነሥርዓት ላይ የማኔጅመንት አባላትና የባንኩ ሠራተኞች፣ የተገኙ ሲሆን፣ በልዩ ልዩ ሁነቶች መርሐግብሩ ተከናውኗል።

Phone:
+251-912345678
Number of Branches:
233
Established Date:
November 10, 1994
Swift Code
AWINETAAXXX