Menu Close

የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የቦርድ አባላት ሥራ ጀመሩ

በቅርቡ ወደ ሥራ እንደሚገባ ይጠበቅ የነበረውን የካፒታል ገበያ ባለሥልጣንን የሚያገለግሉ ስድስት የቦርድ አባላት ኅዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም. መሾማቸው ይታወቃል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ የተሾሙት የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የቦርድ አመራር አባላት ሥራ ጀመሩ።

በቅርቡ ወደ ሥራ እንደሚገባ ይጠበቅ የነበረውን የካፒታል ገበያ ባለሥልጣንን የሚያገለግሉ ስድስት የቦርድ አባላት ኅዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም. መሾማቸው ይታወቃል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል።

ሌሎቹ የቦርዱ አባላት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድምአገኝ ነገራ፣ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ታዬ፣ ከተመድ የካፒታል ዴቨሎፕመንት ኢትዮጵያ ጽሕፈት ቤት ደግሞ (ዶ/ር)ኢዮብ ተስፋዬ ፣የሒሳብና የኦዲት ቦርድ ዋና ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ሒክመት አብደላ፣ የሴሬብሩስ ፍሮንቲየርስ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ ኃይለ ሚካኤል እና የአዲስ አበባ ዩነቪርሲቲ መምህር አቶ አባተ አበበ ናቸው፡፡

ከኅዳር 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ የባለሥልጣኑ የቦርድ አባል ሆነው እንዲሠሩ የተመደቡት እነዚህ የቦርድ አባላት ማክሰኞ ኅዳር 27 ቀን 2015 የመጀመሪያ ስብሰባቸውን አካሂደው ሥራቸውን ጀምረዋል።

እነዚህ ተሿሚዎች በቦርድ አባልነት የተሰየሙት በካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1248 /2013 መሠረት ሲሆን፣ በአዋጁ መሠረት የቦርድ አባላቱ የሥራ ዘመን አምስት ዓመት እንደሆነ ተደንግጓል፡፡

በአዋጁ መሠረት የካፒታል ገበያ ማቋቋም ያስፈለገው ካፒታል በማሰባሰብ፣ የገንዘብ ሥርዓቱን በአዲዲስ ፈጠራዎች በመደገፍ እና የኢንቨስትመንት ስጋቶችን የመጋራት አሠራርን በማስፋፋት የአገሪቱን ኢኮኖሚ ልማት ለመደገፍ እንዲቻል ነው። በተጨማሪም በሀገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ላይ  የሚፈጠሩ መዋቅራዊ ስጋቶችን ለመለየት፣ ለመከላከልና  ለመቀነስ በካፒታል ገበያ ላይ ጠንካራ የቅርብ ክትትልና የቅኝት ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት በማስፈለጉ መሆኑን በአዋጁ ተደንግጓል።

More Posts

የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬና ጤናማ የፋይናንስ ሥርዓት እንዲኖር ይሠራል

የተረጋጋ ዋጋና የውጭ ምንዛሬ እንዲሁም ጤናማ የፋይናንስ ሥርዓት የማክሮኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት በመሆናቸው የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ እነርሱ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ አዲሱ የባንኩ ገዥ አቶ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ ገለጹ፡፡ ከፋይናንስ ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች ጋርም በዘርፍ የ 6 ወር አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

የባንኩ ሠራተኞች 127ኛውን የአድዋ ድል በዓል አከበሩ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሠራተኞችና የማኔጅመንት አባላት 127ኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት አከበሩ። የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በባንኩ አዳራሽ በተከናወነው ሥነሥርዓት ላይ የማኔጅመንት አባላትና የባንኩ ሠራተኞች፣ የተገኙ ሲሆን፣ በልዩ ልዩ ሁነቶች መርሐግብሩ ተከናውኗል።

Phone:
+251-912345678
Number of Branches:
233
Established Date:
November 10, 1994
Swift Code
AWINETAAXXX